ሀበጋር ክዊዝ
““ሀበጋር ክዊዝ” የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የሚካሄድና አንድ ሰዓት የሚፈጅ ፕሮግራም ሲሆን በዋናነት ወጣቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የሲቪክ ትምህርትን ከተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ጋር አጣምሮ የሚያቀርብ
ቢሯችን ለማከናወን ያቀደውን የእውቀት ግንባታ ሥራዎቹን የተሳካ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ጋር ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ይህም በየሳምንቱ ለአንድ ሰዓት “ሀበጋር ክዊዝ” የተሰኘውን የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በአገር አቀፍ ደረጃ በቴሌቭዥን እንዲተላለፍ የአየር ሰዓት አስገኝቶታል።
በተጨማሪም ቢሯችን ከአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን በዚህም አጠቃላይ የጥያቄና መልስ ውድድሩ በቤተ-መጻሕፍቱ ውስጥ እንዲካሄድ አስችሏል።
የውድድሩ ይዘቶችም የኢትዮጵያን ታሪክና ሥነ-ጽሑፍ፣ ሕገ-መንግሥታዊ መብቶችና ግዴታዎችን፣ የፍትሕ አስተዳደርን፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታንና ሰብአዊ መብቶችን፣ እንዲሁም አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን የሚያካትቱ ናቸው፡፡
የጥያቄና መልስ ውድድሩ ትኩረት የሚያደርገው በኢትዮጵያ ታሪክና ሥነ-ጽሑፍ፣ ሕገ-መንግሥታዊ መብትና ግዴታዎች፣ በፍትሕ አስተዳደር፣ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ሰብአዊ መብቶች፣ እንዲሁም አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡
Habegar Quiz
የውድድሩ መዋቅር
“ሀበጋር ክዊዝ” የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በተለያዩ ዙሮች የተከፋፈሉ አሳታፊ እና ልዩ የሆኑ ጥያቄዎችን ይዞ የቀረበ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ፕሮግራም ነው።
የጥያቄዎቹ ባህሪይና ይዘት ለእያንዳንዱ ኩነት ከተመረጠው ዋና ጭብጥ (Theme) ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ የተቀረጸ ነው።
በዚህም መሠረት ውድድሩ የሚከተሉትን የጥያቄ ዙሮች ተከትሎ ለተወዳዳሪዎቹ ይቀርባል፦
QUIZ STRUCTURE

